Monday, July 8, 2019

ስለ ሼህ መሐመድ አላሙዲ(ሼሁ): ከ 200 አመት በፊት የተተነበየ - Fulfilled Prophecy of Sheik Hussein Jibril


Prophecy about Sheik Mohammed Al Amoudi told 200 years ago by shiekh hussen jibril

ስለ ሼህ መሐመድ አላሙዲ(ሼሁ):
ከ 200 አመት በፊት የተተነበየ:
በሸህ ሁሴን ጅብሪል፡፡


  "ግርግር ተነስቶ ፡ በሀበሻ መሬት
    ይሄ ሀብታም ጎበዝ ፡ ሲያመልጥ አየሁት
    አሳስቦኝ ሳይሆን ፡ እንዲያዉ በድንገት..."
   
Mohammed-Al-Amoudi

Prophetic Poems of Ethiopian Sheik Hussein Jibril

Sh Husen Gibril Prediction About Sheik Mohammed Ali Al Amoudi

"The Sheik" of Ethiopia


   አታበቅለዉ የላት የወሎ መሬት
   ሲያንዛብብ አየነው ሲመጣ ድንገት
   ያልተገመተ ሰው ያልጠረጠሩት
   ትልቅ ባለጸጋ በገንዘብ በሀብት
   ገንዘብ ተሸክሞ ገንዘብ ተጭኖት
   የገንዘብ ረግረግ አረንቋ ውጦት
   ቢሰጠዉ ቢረጨዉ የማያልቅ ንብረት
   ታይቶ ያልታወቀ ባበሻ መሪት
   ይሄ ሰዉ ይመጣል እንድትጠብቁት

   


   እጁ ረጅም ሆኖ ፡ ታየኝ ሲጎተት
   በአፍሪካም በእስያም ፡ በአውሮፓ መሬት
   እንደህል ሲዘራ ፡ ገንዘብ እንዳዝሪት
   እዉነት ከሠው በላይ ፡ ደክሞ ነው ሰርቶት?
   አላህ ሰጦት እንጂ ፡ እንትፍ ብሎለት
   አበሻን ባዉሮፓ ፡ ሲያሳዉቃት
   በድህነት ብቻ ፡ ነበር የሚያዉቋት
   ለህዝቡ መከታ ፡ ለሀገር ኩራት
   ለኢትዮጽያ ምሠሶ ፡ አሙዲ ሆነላት
   
   እጁ ዘራፍ ቸር ነው ፡ ገንዘብ ለመስጠት
   እንኳን ለወዳጁ ፡ ያበላል ጠላት
   ስንቱን ሠው ረዳው ፡ ስንቱን ቆመለት
   ስንቱን ሠው አወጣው ፡ ከማጥ ድህነት
   በተጨነቀበት ፡ በችግሩ ወቅት
   
   አሁን ነገርኳችሁ ፡ ኋላ እንድታዩት
   ሃበሻ ላይ ቁሞ ፡ አውሮፓን ነካት
   አፍሪካን ጨብጦ ፡ ኢስያን ዳሰሳት
   እያገላበጠ ፡ ላይ ታቿን አያት
   አውሮፓና ኢስያ ፡ አርሂቡ እያሉት
   አረቦች በወዲያ ፡ እጁን ጎተቱት
   የኛ ነህ እያሉ ፡ ዘር ስላለበት
   በራቸዉን ከፍተዉ ፡ ግባልን አሉት
   ለሁሉም ይበቃል ፡ እሱ ምን ገዶት
   እያወቀው መጣ ፡ የአለም መንግስታት
   ታየኝ ሲቀበሉት ፡ እጅ ሲነሱት
   ገባ ቤተመንግስት ፡ ሊያስተናግዱት
   እንደ ባለስልጣን ፡ እንደ መኳንንት
   ለክብሩ ሲሰጠዉ ፡ እሻን ሽልማት
   የሚንጠለጠል ነው ፡ በደረት ባንገት
   እንዲህ ነዋ ገንዘብ ፡ እንዲ ነዋ ሀብት
   ፍርዱንም ፈረድነዉ ፡ መሰከርንለት
   ሙስሊም በመሆኑ ፡ እኔም ወደድኩት
   በፈጣሪ ያምናል ፡ በአላህ አንድነት
   
   እስላሞች ደጋግመዉ ፡ እያበሳጩት
   በእስልምና በኩል ፡ ስሙን ሲያጠፉት
   እያስከፉት መጡ ፡ ቅር እያሰኙት
   የማይሉት የለም ፡ የማያስወሩት
   የማይጭሩት የለም ፡ የማይሞክሩት
   ቀዳዳ ፍለጋ ፡ የሚገቡበት
   ሙስሊሙ እንዲጠላው ፡ እንዳይጠጉት
   እንደጥፋተኛ ፡ ሊያስፈርዱበት
   ያዉም የረዳቸዉ ፡ በጁ የበሉት
   እስኪ አንዳንድ ጊዜ ፡ እናዉራ ዉነት
   መቼም አዉቁ አጥፊ ሠው ፡ አይዋጥለት
   
   በክርስቲያኑም ህዝብ ፡ በሙስሊሞች ቤት
   ዉሸት ልምድ ሆኖአል ፡ እንደ ሃይማኖት
   ይከታተለዋል ፡ ሰው እንደ ትምህርት
   ይሄ ጥሩ ነው ወይ ፡ ሰዎት ይፍረዱት
   ስጋዉን እንደ ጫት ፡ እያላመጡት
   ይሄንን ደህና ሰው ፡ ይሀን አዛዉንት
   መንግስትን ይረዳል ፡ ብለዉ የሚያሙት
   በገዛ ገንዘቡ ፡ ባፈራው ንብረት
   ምን እንዲሰራ ነው፡ የሚፈልጉት?
   ከመንግስት ይጣላ ? ሓብቱን ይዉረሱት?
   እንደወንጀለኛ ፡ ካገር ያባሩት?
   ይግባ ወይ በረሃ ? ጫካ ይሸፍት?
   ታጥቆ ተደራጅቶ ፡ ወደ ጦርነት
   በየቦታው ጥሎት ፡ ይሄን ሁሉ ሓብት
   ይሄን ነው ወይ ለሱ ፡ የምትመኙት?
   መጥፎ ሆኖ ነዉ ወይ ፡ ከገዥ መስማማት?
   ባለስልጣን ናቸው ፡ ባለሰራዊት
   ደህና አድርጎ ያውቃል ፡ እንደሚጎዱት
   
   ታይቷችሁ ከሆነ ፡ ይሄ እንደስተት
   ከሱ ቦታ እናንተ ፡ ሆናችሁ እዩት
   ወይ ታመሰግኑት ፡ ወይ ታነዉሩት
   ከሁለት አንዱ ቃል ፡ መባል አለበት
   ያን ጊዜ ይለያል ፡ ዉሸቱም እዉነት
   እኔ ጠየኳችሁ ፡ መልሱን መልሱት
   እኔ እንኳ አልገኝም ፡ ለሱ ንገሩት
   
   እስኪ ሁላችንም ፡ እናስብበት
   በዩሃንስ ጊዜ ፡ ቢሆን ይሄ ወቅት
   ሰይጣን አይስማ እንጂ ፡ አይምሰልበት
   እንኳን ሙስሊም ሆኖ ፡ ከቶም ባለሃብት
   ስሙ እንደዚህ ገኖ ፡ ዩሃንስ አይቶት
   እንዴት ይሆን ነበር ፡ እስኪ ገምቱት
   ይተዉት መስሎሃል ፡ አንቀው ሳይገሉት
   ስንቱን ኡለማ ነው ፡ አርደዉ የጣሉት
   ሳይታወቅ ቦታዉ ፡ የወደቀበት
   ያንዱ እንኳ ሠው ስሙ ፡ ሳይፃፍለት
   ጠፍቶ ነዉ ወይ ባገር ፡ ቀለም ወረቀት?
   ምናለ ቢፅፉት ፡ ሰዎች ቢያነቡት
   ወይንስ የሚፅፍ ሰው ፡ የለም በዛ ወቅት?
   አሳዝኖት ሳይሆን ፡ እንዲያዉ ለትዝብት
   
   ዩሃንስ ነቢ ነው ፡ በክርስቲያን ፊት
   ነገስታቱን በልጦ ፡ ሳይሆን በሹመት
   ይጥፋ ስላለ ነዉ ፡ የእስላም ሀይማኖት
   ተዳፈርኩኝ መሰል ፡ እኔ አበዛሁት
   የእስላሞቹን በጥቅስ ነካሁት
   ደግሞ እንዳያገረሽ ፡ ሲቀረፋፈት
   ዝም ብዬ ልለፈዉ ፡ እንዳልሰማሁት
   ይቀመጥ ከሆዴ ፡ እዛዉ ይሸብት
   እኔስ እሄዳለዉ ፡ ወደዛኛዉ ቤት
   አዘንኩ ለእናንተ ፡ ለምትቀሩት
   
   ህስልና ነዉ እንጂ ፡ በሰው ላይ መቅናት
   እንኳን ተሸክሞ ፡ ይሄን ሁሉ ሐብት
   ሰው ለጠባብ ቦታ ፡ ለትንሽ መሬት
   ለአንገቱ ማስገቢያ ፡ ለመኖሪያ ቤት
   ይባክን የለም ወይ ፡ ገንዘብስ ጉልበት
   ለመኖር ከሆነ ፡ ሰው ለመሰንበት
   ይሄንን ሰዉዬ ፡ ምነዉ ብትተዉት
   መስሎአችሁ ከሆነ ፡ የምታጠቁት
   ነግሬአችኋለዉ ፡ እንደማትችሉት
   
   ያስቡም ነበረ ፡ ሃብቱን ሊዘርፉት
   አላጋለጠዉም ፡ ረቢል ኢዘት
   ተካዱስ በሳቸዉ ፡ ገና ሲዶለት
   የሚያፍሩም ሞልተዋል ፡ አይኑን ለማየት
   የሰማ መስሎአቸው ፡ ወሬ በድንገት
   ከዳተኛ እንዲህ ነዉ ፡ ሁል ጊዜ ዉርደት
   
   ከእስላሙ ክርስቲያን ፡ ነዉ ያወቀበት
   የሚፈልገዉን ፡ ልቡን ያገኙት
   ሽሬታ ማወቅ ነው ፡ እህል ስትሸምት
   እነሱም ተጠቅመዉ ፡ እሱም ደስ ብሎት
   ከፈለጉት በላይ ፡ ነዉ ያተረፉት
   አዱኛ እንደዚህ ናት ፡ ሰው ካወቀባት
   ምን ኸይር ብትሰራ ፡ አይጠፋም ስህተት
   ያኸይራዉንማ ፡ ማን ካለሱ አውቆት
   መታጠቅ ይሻላል ፡ መደረጃጀት
   ገና ሳንለቃት ፡ የዱንያን መሬት
   ለዚህ ሙስሊም ሀብታም ፡ ዱአ እናርግለት
   ምርቃን ጥሩ ነዉ ፡ ሰዉ ካዘንክለት
   
   ገና ፍርድ ስጀምር ፡ አስቀድሜ ጠዋት
   አይችልም ብያለሁ ፡ ሰዉ ለሰዉ መስጠት
   እሱስ ማን ሰጦት ነዉ ፡ ከየት አግኝቶት
   ለምኖ ነዉ እንጂ ፡ ካላህ ግምጃ ቤት
   አላህ ከፈቀደ ፡ ትንሽ ዳረጎት
   ይሄ ብልጥነት ነዉ ፡ ለባርያ ኩራት
   ለምኖ ለለማኝ ፡ ነዉ እንዳትረሱት
   አሁን ልመርቀዉ ፡ ቃሌን አዳምጡት
   ሰጪን አላህ ይስጠዉ ፡ አይቀንስበት
   አላህ ይጨምረዉ ፡ በሐብት ላይ ሐብት
   በልቶ እንኳን ያበላል ፡ በቸገረ ወቅት
   ነገም ያቀማጥለዉ ፡ ወስዶ በጀነት
   ሳያጠፋ አይቀርም ፡ ሰዉ ሳይሳሳት
   የነ ኢዙ ጌታ ፡ የነ ጀበሩት
   እሱ አፉ ላለው ሰው ፡ ማንስ ጠይቆት
   
   ምንስ ልትጎዳው ነዉ ፡ ያንድን ሰው ስህተት
   ከስልጣኑ አይቀንስ ፡ አይጨምርለት
   ቢምርም ቢቀጣም ፡ ስልጣን የአላህ ናት
   ኢትዮጵያን ይወዳል ፡ ይሄ ሰው በዉነት
   አላህም ስለዚህ ፡ አይጨክንበት
   ግርግር ተነስቶ ፡ በሀበሻ መሬት
   ይሄ ሀብታም ጎበዝ ፡ ሲያመልጥ አየሁት
   አሳስቦኝ ሳይሆን ፡ እንዲያዉ በድንገት
   ይገርማል ሲያስቡት ፡ ጉድ አጃኢበት
   ምን ሊጠቅመኝ ይሆን ፡ የምወሻክት
   እሱም አያገኘኝ ፡ እኔ አልደርስበት
   ተራርቀን ታየኝ ፡ በመቶ ሃምሳ አመት
   ታዘበኝ ካልሆነ ፡ እንደፈረድኩት
   አንዳንድ እኳን ብታይ ፡ የሆነ ስህተት
   ዘንግቼዉ ይሆናል ፡ ያልተናገርኩት
   ስህተት መች ይጠፋል ፡ ከሰዉ አንደበት
   ፈጣሪ ብቻ ነዉ ፡ የማይሳሳት
   ባለቤቱ እሱ ነዉ ፡ የአላህ ናት እዉቀት
   ለሰዉ ልጅ አይጠቅምም ፡ ሂስል እና ኩራት
   ያልሰሙትን ማዉራት ፡ ዋሽቶ ማስዋሸት
   ከዚህ ይጠብቀን ፡ ጌታችን በዉነት
   ሁላችን ለማኝ ነን ፡ ከአላህ ራህመት
   እንዳያሳፍረን ፡ ነገም ከሱ ፊት